You are currently viewing ምክር ቤቱ የካርበን ገበያ ረቂቅ አዋጅን አጸደቀ

ምክር ቤቱ የካርበን ገበያ ረቂቅ አዋጅን አጸደቀ


የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 29ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ የካርበን ገበያ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጽድቋል፡፡
በምክር ቤቱ የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ በቋሚ ኮሚቴው የተዘጋጀውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡
ሀራችን በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ የምትጎዳ ሃገር እንደመሆኗ የካርበን ገበያ ስትራቴጂ ወደ ተግባር ለመለወጥ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
የፓሪሱን ስምምነት ጨምሮ ሀገራችን የፈረመቻቸውን ዓለም አቀፍ ውሎችና የገባቻቸውን የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀት ቅነሳ ቃል ኪዳኖች ተግባራዊ ለማድረግ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የሚያግዝ አዋጅ ስለመሆኑ ሰብሳቢው ገልጸዋል፡፡
አዋጁ ቀደም ሲል ያለበቂ የአሰራር ሥርዓት ሲተገበር የነበረው የግብይት ሂደት በግልፅ የህግ ማዕቀፍ እንዲመራ ለማድረግና ተበታትነው የነበሩ ደንብና መመሪያዎችን ወደ አንድ ወጥ የህግ ማዕቀፍ በማጠቃለል የአሰራር ወጥነት፤ ግልፅነት እና የአገልግሎት ቅልጥፍና ማስፈን የሚያስችል መሆኑን አቶ ደሳለኝ ባቀረቡት የውሳኔ ሀሳብ አስገንዝበዋል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት በበኩላቸው አዋጁን አስፈላጊነት በስፋት ያነሱ ሲሆን፤ በኢትዮጵያን የካርበን ገበያ የህግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱ ለአረንጓዴ አሻራ ኢንቨስትመንት እንዲሁም ለቴክኖሎጂ ሽግግር ምቹ ሁኔታን መፍጠር እንደሚያስችል ጠቅሰዋል።
በመጨረሻም ረቂቅ አዋጁ የኢትዮጵያ የካርበን ገበያ አዋጅ ቁጥር 1436/2018 ሆኖ በአንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምዕ ጸድቋል። (Source EBC)

Leave a Reply