የኢትዮጵያ የደን ልማት ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በላከው መግለጫ ዓለም እያጋጠማት ያለውን የአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቋቋም መፍትሄ ተደርጎ የተወሰደውን ተፈጥሮን መፍትሄ ያደረጉ አማራጮች መጠቀም መነሻ በማድረግ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተመራው አረንጓዴ አሻራ እየተገበረች መሆኑ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም በተራቆቱ መሬቶች ማገገሚያ አረንጓዴ አሻራ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ታይቶ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መመራቱ ኢትዮጵያ በዓለምአቀፍ ደረጃ የምታቀርባቸው ፕሮፖዛሎች ተቀባይነት እንዲኖራቸው ማድረጉም ተነስቷል፡፡
በዚህም የአየር ንብረት ኢንቨስትመንት ፈንድ(ሲ አይ ኤፍ) ቦርድ በአሜሪካ ዋሽንግተን ስብሰባ አካሂደዋል፡፡
በዚህም በኢትዮጵያ ደን ልማት የቀረበለትን 37 ሚሊየን አሜሪካ ዶላር ፕሮጀክት ጸድቋል፡፡ FBC