በምስራቅ በለሳ ወረዳ ጉዋላ ከተማ በሚገኘው የ “Regrade II” ፕሮጀክት ውስጥ በጥበቃ ባለሙያነት ሲያገለግል የነበረው ባልደረባችን አቶ አዲኖ ምትኩ ያለጊዜው ከዚህ አለም በሞት በመለየቱ ድርጅታችን ኢትዮ ዌትላንድስ ኤንድ ናቹራል ሪሶርስ አሶሴሽን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል።
አቶ አዲኖ በድንገተኛ ህመም አርብ ሰኔ 14 ቀን 2025 አመሻሽ ላይ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል። የቀብር ስነ ስርአቱም በትውልድ ቦታው ወዳጅ ዘመዶቹ እና የአካባቢው ነዋሪ በተገኙብት ቅዳሜ ሰኔ ሰባት ቀን 2017 ዓ.ም ተፈጽሟል። ሀምሌ 24 ቀን 1986 ዓ.ም የተወለደው የ30 አመቱ ወጣት አዲኖ እ.ኤ.አ. ከሴፕቴምበር 3, 2023 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ድርጅታችን ኢትዮ ዌትላንድስ ኤንድ ናቹራል ሪሶርስ አሶሴሽን EWNRA ተቀላቅሎ በመስራት ላይ ነበር።
አቶ አዲኖ ከእኛ ጋር በነበረው አጭር ጊዜ ውስጥ ስራውን በትጋት በመወጣት ይታወቃል።
አዲኖ የሚወዳቸውን ሚስቱን እና አንድ ልጁን ትቶ በመሄዱ የተሰማንን ከፍተኛ የልብ ስብራት እየገለጽን ለቤተሰቦቹ፣ ለጓደኞቹ እና በአጠቃላይ ለሚያውቁት ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን። የ EWNRA ቤተሰብ በዚህ አሳዛኝ ክስተት ከልብ ያዝናል።
ይህ ለእኛ እንደ ድርጅት በጣም አስቸጋሪ ወቅት ነው። ባለፉት 24 ዓመታት ውስጥ ሶስት ሰራተኞችን አጥተናል እና እያንዳንዱ ሞት ዘላቂ አሻራ ጥሏል። የአዲኖ ህልፈት የሥራ ባልደረባችንን ማጣት ብቻ አይደለም። ይልቁን ትልቅ ዋጋ የነበረው የድርጅታችን እና የማህበረሰቡ አካል ነበር።
ነፍሱን በገነት ያኑርልን።